Why Abugida?
qualified teachers
We employ only highly skilled teachers with experience in teaching children.
cultivators of creativity
Abugida Academy offers programs to encourage your child's creative thinking.
multi-language environment
We offer programs in English and Amharic.
Abugida Academy, አቡጊዳ
እንኳን ልጆች ቅድሚያ አግኝተው ወደሚያድጉበት ወደ አቡጊዳ አካዳሚ በደኅና መጡ!
አቡጊዳ አካዳሚ ስለ ልጆች በትምህርት ላይ የተመሠረተ እድገት ለመወያየት በመገኘትዎ በጣም ደስተኛ ነን። አቡጊዳ አካዳሚ ልጆች በትምህርት ብልጽግና ተመርኩዘው በአካልና በማኅበራዊ ሕይወት እያተበረታቱ እንዲያድጉ ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋል። አካዳሚያችን ልጆች በምክንያትዊና በፈጠራ የሚመራ ዕውቀት እንዲኖራቸው በትጋት ይሠራል። ወላጆች የተወደዱ ልጆቻቸውን በአቡጊዳ አካዳሚ አስቀምጠው ሲሄዱ ምቾት ይሰማቸዋል። እያንዳንዱ ቀንን ወደ ውጤታማ ዕለት በመቀየር አቡጊዳ አካዳሚ ወላጆች ከሚጠብቁትና ከሚገምቱት በላይ ይሠራል። ዕውቀት፡ አካል ብቃት፡ ማኅበራዊ፡ ምክንያታዊና ትምህርት ነክ ተግባራት የአቡጊዳ አካዳሚ መለያዎች ናቸው። ልጆች ወደ ሚቀጥለው የትምህርት ደረጃ ከመድረሳቸው አስቀድሞ የተለየና የተሟላ ዝግጅት በማድረግ በዕድሜ በተከፋፈለ የትምህርት መስፈርት የፊደላትን ድምጽ በሚገባ እንዲለዩ፡ የንባብ፡ የሒሳብ፡ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክኅሎታቸውን አዳብረው እንዲገኙ ማድረግ የአቡጊዳ አካዳሚ ተቀዳሚ ራዕይ ነው። ልጆቻቸው የአማርኛ ቋንቋንና ስለ ኢትዮጵያ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለሚሹ የተለየ ዝግጅ አድርገናል። አቡጊዳ አካዳሚ ዕድሜያቸው አንድና ከአንድ በላይ የሆኑ ሕፃናትንና ልጆችን በተጨማሪም ከትምህርት ቤት በኋላ መቆየት የሚፈልጉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል። የቱቶር ፕሮግራማችን ውጤት ተኮር ሆኖ በሁሉም የትምህርት ዘርፎች ላይ ያተኮረና ለየት ያለ ነው። አቡጊዳ አካዳሚ ውስጥ ልጆች በትምህርት ብልጽግናና በራስ በመተማመን ላይ የተገነባ ማንነት ይዘው ወደሚቀጥለው ደረጃ እንዲያልፉ ያላሰለሰ ጥረት ይደረጋል።
ስለጎበኙን ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን!
ትግስት ባቻ
የአቡጊዳ አካዳሚ ዳይሬክተር
News & Updates
-
11501 Plano Road, Dallas, TX 75243